ከሳኡዲ አረቢያ በ2ኛ ዙር 438 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

መጋቢት 21/2014 (ዋልታ) ከሳኡዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 438 ዜጎች በሁለተኛ ዙር ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በሳኡዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ብሔራዊ አስፈፃሚ ኮሚቴ በማዋቀር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በተለያየ ደረጃ ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል።
በዚህም መሠረትም በዛሬው ማለዳ የመጀመሪያው ዙር ተመላሾች የገቡ ሲሆን ከሰዓት በኃላም በሁለተኛው ዙር በረራ 438 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ተመላሾቹ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱም ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡