ጠ/ሚ ዐቢይ በኦቦ ገላሳ ዲልቦ ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

Recommendationመጋቢት 22/2014 (ዋልታ) የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር የነበሩት ኦቦ ገላሳ ዲልቦ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሐዘናቸውን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ኦቦ ገላሳ ዲልቦ ማረፋቸውን በመስማቴ እጅግ አዝኛለው፤ ከተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት እና እኩልነት ታግለዋል ሲሉ ገልጸዋል።

በቅርቡ በለውጡ አመራር በተደረገላቸው ግብዣ የሰላማዊ ትግል ጉዞ መርጠው ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ መታገል ከመጀመራቸውም ባሻገር በ2013 ዓ.ም ምርጫ በግል ተወዳድረው የፓርላማ አባል ለመሆንም ችለዋል።

በትግል ውጣ ውረድ ውስጥ የገጠማቸውን በጎ እና ክፉ ለማሄስ እና ወጣቶች ከሁለቱም እንዲማሩ ለማድረግ ይተጉ ነበር ብለዋል።