የሀረሪ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

መጋቢት 22/2014 (ዋልታ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር አንደኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው የስድስተኛው አንደኛ መደበኛ ጉባዔን ቃለ ጉባዔን እንደሚጸድቅና የአስፈጻሚ አካላት የስድስት ወራት አፈጻጸም፣ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2012 እና 2013 ዓ.ም የሴክተር መስሪያ ቤቶች የኦዲት ግኝት ፋይናንሻል ሪፖርት እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

ጉባዔው በሚኖረው ቆይታ የምክር ቤቱ የተሻሻለውን የአሰራር እና አባላት ሥነ ምግባር ደንብ መርምሮ ያፀድቋል ተብሎም ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪም የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አዋጅ ማሻሻያ እና የጠቅላይ አቃቢ ህግ ቢሮ ማቋቋሚያና ተግባርና ስልጣንን የሚወስነውን አዋጅንም እንደሚያፀድቅ ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW