ጄኔራል አበባው ታደሰ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር ተወያዩ

መጋቢት 22/2014 (ዋልታ) የሀገር መከላከያ ሰራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ሌተናል ጄኔራል ቶይ ቻኒይ ሬይት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ የተመራ የልዑካን ቡድን በጁባ የሥራ ጉብኝት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በዚህም ከደቡብ ሱዳኑ አቻቸው ሌተናል ጄኔራል ቶይ ቻኒይ ሬይት እና ቡድናቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡
የኢትዮጵያው ወገን በሎጂስቲክስና በአቅም ግንባታ ጉዳዮች ለደቡብ ሱዳን ወገን ድጋፍ ለማድረግና ተሞክሮ ለማጋራት እንዲሁም የሁለቱ አገራት የድንበር አካባቢ ፀጥታና ደኅንነትን ከማረጋገጥ አኳያ በትብብር ለመሥራት ከስምምነት መደረሱን በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!