51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በዛሬው እለት ይጠናቀቃል

መጋቢት 24/2014 (ዋልታ) 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 10 የፍፃሜ ውድድሮች ተደርገውበት በዛሬው እለት ይጠናቀቃል።

51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከመጋቢት 19 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት በሀዋሳ ዓለም ዐቀፍ ስታዲየም እየተካሄደ ይገኛል።

በሻምፒዮናው ከዘጠኝ ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ ከክለቦችና ተቋማት የተውጣጡ አትሌቶች እየተካፈሉ ይገኛሉ።

የውድድሩ መርሃ ግብር ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን በ10 የፍፃሜ ውድድሮች ከፍተኛ ፉክክር የሚደረግ ይሆናል።

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW