በሀረሪ ክልል የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ተገለጸ

መጋቢት 26/2014 (ዋልታ) በክልሉ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች እናጠናክራለን ሲሉ የሀረሪ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡

ርዕሠ መስተዳድሩ በክልሉ በተለያዩ ስፍራዎች እየተገነቡ የሚገኙ ሼዶች፣ የወጣቶች ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የባህል ማዕከል ማስፋፊያዎችና የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክቶችን ተመልክተዋል።

ርዕሠ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት በክልሉ ግንባታቸው ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የልማት ሥራዎች በአፋጣኝ ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ ይገባል።

ግንባታቸው በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችም ለጉዳት እየተጋለጡ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በመሆኑም የግንባታዎቹ በፍጥነት ማጠናቀቅ የሥራ እድልን ከመፍጠር ባሻገር ወጣቶች አልባሌ ስፍራ እንዳይውሉ ትልቅ እገዛ እንደሚፈጥር መናገራቸውን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡