ከየትኛውም ዓለም መጥተው ኢድን አብረውን የሚያከብሩትን ሁሉ ልንቀበላቸው ተዘጋጅተናል – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እንድሪስ

ሀጂ ዑመር እንድሪስ

መጋቢት 27/2014 (ዋልታ) ከየትኛውም ዓለም መጥተው ኢድን አብረውን የሚያከብሩትን ሁሉ ልንቀበላቸው ተዘጋጅተናል ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እንድሪስ ገለጹ፡፡

ከመላው ዓለም በመሰባሰብ ኢድን በጋራ ለማክበር የቀረበው ጥሪ አንድነትና ትብብራችንን በተግባር የምናሳይበት ልዩ ታሪካዊ አጋጣሚ ይሆናል ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ በድርቅና ጦርነት የተጎዱ ወገኖችን በመተጋገዝ ድጋፍ ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል ብለዋል።

በምክር ቤቱ የመስጂዶችና የአውቃፍ ዘርፍ ኃላፊ ሸህ መሀመድ ሀሚዲን (ዶ/ር) በበኩላቸው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው በአገራቸው ተገኝተው ሲያከብሩ ምክር ቤቱ ደስተኛ ነው ብለዋል፡፡

በዓሉን በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በሀገራቸው በመሰባሰብ ማክበራቸው ይበልጥ አንድነትና ወንድማማችነታቸውን የሚያሳዩበት እንደሆነ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!