በሸኔ ላይ እየተወሰደ ባለ እርምጃ በርካታ የቡድኑ አባላት መደምሰሳቸው ተገለጸ

መጋቢት 29/2014 (ዋልታ) በአሸባሪው የሸኔ ታጣቂዎች ላይ እየተወሰደ ባለ እርምጃ በርካታ የቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ።

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የ30 ቀን ዕቅድ መሰረት በአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የክልሉ የፀጥታና አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ አስታውቀዋል፡፡

ኮሎኔል አበበ በተጀመረው ኦፕሬሽን በርካታ የሽብር ቡድኑ አባላት የተደመሰሱ መሆናቸውን ገልጸው የተመዘገቡ ድሎች በዝርዝር ለሕዝብ ይፋ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡

አሸባሪው ቡድን ኦሮሚያን የብጥብጥ ቀጣና በማድረግ አገር ለማፍረስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን ማፍረስ ከምናባዊ እሳቤና ከቀን ቅዥት ስሌት በዘለለ መቼም ቢሆን ሊሳካ የማይችል የሴረኞች ህልም ነው ብለዋል።