የባለሥልጣኑ የቦርድ አባላት ሹመት ፀደቀ

መጋቢት 29/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ አባላት ሹመትን አፀደቀ፡፡

ምክር ቤቱ ባለሥልጣኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 1238/2ዐ13 መሠረት ነው ያፀደቀው፡፡

በዚህም መሰረት

  1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ሰብሳቢ
  2. አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ከቱሪዝም ሚኒስቴር፤ አባል
  3. አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ከዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል፤ አባል
  4. አጋረደች ጀማነህ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ አባል
  5. በድሉ ዋቅጀራ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ አባል
  6. መሣይ ገ/ማሪያም (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ አባል
  7. ወዳጀነህ ማዕረነ (ዶ/ር) አማካሪ፤ አባል
  8. ቀሲስ ታጋይ ታደለ ከሃይማኖት ተቋማት፤ አባል
  9. ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ከሃይማኖት ተቋማት፤ አባል ሆነው በውሳኔ ቁጥር 8/2ዐ14 በ11 ተቃውሞ እና በ17 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምፅ የፀደቀ ሲሆን በዚህም መሠረት ተሿሚዎቹ ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።