በአዲስ አበባ ከ3 ሺሕ በላይ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

መጋቢት 29/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ በበጀት ዓመቱ 3ኛ ሩብ ዓመት ከ3 ሺሕ በላይ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የከተማዋ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ ሶስተኛ ሩብ ዓመት 2 ሺሕ 698 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት አቅዶ 3 ሺሕ 5 ፈቃዶችን መስጠቱ ተመላክቷል፡፡

አፈጻጸሙ 111 በመቶ መሆኑን የገለጸው ኮሚሽኑ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸርም የ8 ነጥብ 6 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ጠቁሟል፡፡

አፈጻጸሙ አዲስ አበባ ላይ ያለው የኢንቨስትመንት ፍሰት አበረታች መሆኑን አመላካች ነው መባሉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW