አየር መንገዱ ለ”ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ተጓዦች የ20 በመቶ ቅናሽ አደረገ

መጋቢት 29/2014 (ዋልታ) የታላቁ ጉዞ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ ሁለተኛ ክፍል የሆነው “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት” ጥሪን ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ጉዞ ትኬት ዋጋ ላይ 20 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።
በዚህም ወደ ሀገር ቤት ተጓዦች ትኬታቸውን ከአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ሚያዚያ 6 እስከ መያዚያ 21፣ 2022 በመቁረጥ እና ጉዟቸውን ከሚያዚያ 25 እስከ ግንቦት 15፣ 2022 ድረስ በማመቻቸት የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ተጓዦቹ ወደ ሀገር ቤት ከመጡ በኋላም በተዘጋጁላቸው ልዩ ልዩ መርኃ ግብሮች ላይ እንዲታደሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡