የአዋሽ 2 – አሰላ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ ጥገና ተጠናቀቀ

ሚያዝያ 2/2014 (ዋልታ) በዘራፊዎች ተቆርጦ የወደቀው ከአዋሽ 2 ወደ አሰላ የተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን በእንጨት ምሰሶ የመተካት ሥራ ተጠናቀቀ፡፡

መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም በዶዶታ ወረዳ እና ጌራ ከተማ አቅራቢያ በተፈፀመው የምሰሶ አካላት ዝርፊያ ሁለት ምሰሶዎች የወደቁ ሲሆን በአካባቢው በከፊል ኤሌክትሪክ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል።

ለቀናት ሲከናወን የቆየው ጥገና ዛሬ በመጠናቀቁ ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ እንደሚከናወን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡