ድጋፍ ለሚሹ የወልዲያ ነዋሪዎች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

ሚያዝያ 4/2014 (ዋልታ) ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በወልዲያ ከተማ ድጋፍ ለሚሹ ከ3 ሺሕ በላይ ወገኖች 10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የምግብና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ለ1 ሺሕ 641 ወላጆቻቸውን ላጡ ህፃናትና አቅመ ደካሞችን በመለየት ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን የፕሮጀክቱ አሰተባባሪ ጋሻው አለባቸው ገልጸዋል።
በድርጅቱ በሁለት ቤተሰብ 120 ኪሎ ዱቄት፣ አራት ኪሎ ስኳር፣ ሁለት ሊትር ዘይት፣ ስምንት ኪሎ ክክ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ተጠቃሚዎቹ ተናግረዋል።
በቀጣይም የሥነ-ልቦና ጥቃት ለደረሰባቸው መምህራን ስልጠና እንደሚሰጥ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ መግለጻቸውን ከሰሜን ወሎ ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።