1 ሺሕ 245 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ

ሚያዝያ 7/2014 (ዋልታ) በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው 1 ሺሕ 245 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾቹ ውስጥ 686 ሴቶች፣ 191 ህጻናትና 368 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ከ9 ሺሕ 700 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከየሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡