ንግድ ባንክ 17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር አሸናፊ ሆነ

ሚያዝያ 9/2014 (ዋልታ) 17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው 17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር 14 ክለቦች ተሳትፈውበታል።

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ውድድር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀዳሚ ሆኖ ጨርሷል።

ሁለተኛ የኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲሆን የኦሮሚያ ፖሊስ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

84 አትሌቶች በተሳተፉበት ውድድር የመጨረሻውን ዙር መገርቱ ኢፋ ከንግድ፣ ዐይነአዲስ ተሾመ ከኢትዮ-ኤሌክትሪከ እና መገርቱ ዓለሙ ከኦሮሚያ ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ በመያዘ አጠናቋል።

ሚኪያስ ምትኩ (ከጅግጅጋ)

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!