ሚያዝያ 9/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የጀመረችው የአረንጓዴ ዐሻራ ጥረት የግብርና ምርታማነትን እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲቻል በርካታ እና ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ መሆኑን አስታወቁ።
የአፈር እና ውኃ ጥምረት ለግብርና ምርታማነት ወሳኝ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንደ ሀገር ለውኃ እና ለአፈር አያያዝ አሠራሮችን ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት በዓለም በውኃ አቅርቦት ማነስ እና በአፈር መሸርሸር የተነሣ የመሬት መራቆት እየተባባሰ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!