በመዲናዋ የእሁድ ገበያ 50 ቦታዎች ላይ መስፋፋቱ ተገለፀ

ሚያዝያ 9/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ የእሁድ ገበያ 50 ቦታዎች ላይ መስፋፋቱ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት እና በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች ያለባቸውን የኑሮ ጫና በመቀነስ ረገድ ጉልህ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል፡፡

አቅርቦቱን በመጨመርና በማስፋፋት ይበልጥ ወደ ሕዝቡ እንዲቀርብ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ስለመሆኑ መግለጻቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል፡፡

ከንቲባዋ የእሁድ ገበያ እንዲስፋፋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ አመራሮችና ምርት አቅራቢዎችን አመስግነዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!