የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመገናኛ ብዙኃን አመራሮች ጋር ምክክር እያካሄደ ነው

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ሚያዝያ 13/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመገናኛ ብዙኃን አመራሮች ጋር በጋራ መስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር እያካሄደ ነው።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ኮሚሽኑ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ጸሎት እንዲያደርጉ በማድረግ ሥራ መጀመሩን አንስተው አሁንም ውጤታማ ሀገራዊ ምክክር ማድረግ እንዲቻል ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመወያየት ግብዓት እየሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል።

የመገናኛ ብዙኃንም ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ስኬታማ እንዲሆን ቁልፍ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ከመገናኛ ብዘኃን ጋር እንዴት በጋራ መስራት ያስችላል የሚለውን መመካከር ያስፈልጋል ብለዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን የምክክር ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እየሄደበት ስላለው ቅድመ ዝግጅትና ትግበራ ገለጻ አድርገዋል።

በመስከረም ቸርነት

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!