ግብረ ኃይሉ የትንሳኤ በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት አጠናቀቀ

ሚያዝያ 13/2014 (ዋልታ) የፌዴራል ፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የትንሳኤ በዓል ያለምንም የፀጥታ ስጋት በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል።

ግብረ ኃይሉ የኅብረተሰቡን ሰላምና ደኅንነት ለማስከበር ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ወደ ስምሪት ገብቶ ተልዕኮውን እየተወጣ እንደሚገኝ ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህ የፀጥታ ማስከበር ሂደት ውስጥ ኅብረተሰቡ በአካባቢው ለሰላም እንቅፋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት የተለመደውን ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ከግብረ ኃይሉ ጎን በመሆን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

የፌዴራል ፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች እና በግዳጅ ላይ ላሉ የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች የመልካም በዓል ምኞቱን አስተላልፏል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW