ዋና ዳኛ በአምላክ ተሰማ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የፔትሮ አትሌቲኮ እኛ ማማሎዲ ሴንዳውንስን ጨዋታ ይመራሉ

ሚያዚያ 14/2014 (ዋልታ) የካፍ ኤሊት ዋና ዳኛ በአምላክ ተሰማ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የአንጎላው ፔትሮ አትሌቲኮ ከደቡብ አፍሪካው ማማሎዲ ሴንዳውንስ የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ ለመዳኘት በካፍ ተመርጠው ደቡብ አፍሪካ ደርሰዋል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አንጎላ ላይ በፔትሮ አትሌቲኮ 2ለ1 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን የመልስ ጨዋታው በደቡብ አፍሪካ ኤፍ ኤን ቢ ስታድየም እንደሚደረግ የሶከር ኢትዮጵያ መረጃ አመላክቷል፡፡