ዛሬ 1 ሺሕ 149 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ

ከሳኡዲ አረቢያ ተመላሾች

ሚያዚያ 14/2014 (ዋልታ) ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺሕ 149 ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከእነዚህ ውስጥ 14 ህጻናት እና 1ሺሕ 135 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ 12 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያዊያን መመለስ መቻላቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW