አምባሳደር አክሊሉ በዱባይ ችግር እያጋጠማቸው ስላሉ ኢትዮጵያዊያን መፍትሄ እንዲፈለግ ጠየቁ

ሚያዚያ 17/2014 (ዋልታ) በዱባይ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ቆንሱል ጄኔራል አምባሳደር አክሊሉ ከበደ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ዱባይ ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ረሺድ አብዱላህ አል ቃሲር አስገብተዋል ።

አምባሳደር አክሊሉ በዚህ ወቅት ለምክትል ዳይሬክተሩ በዱባይ ችግር እያጋጠማቸው ስላሉ ኢትዮጵያዊያን መፍትሄ እንዲፈለግ ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ምክትል ዳይሬክተሩም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ምክትል ዳይሬክተሩ ከቆንሱል ጄኔራሉ ጋር በቅርበት ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።