ከ10 ሺሕ በላይ ሰዎች የተሰተፉበት የኢፍጣር ፕሮግራም በሀላባ ተካሄደ

የኢፍጣር ፕሮግራም በሀላባ

ሚያዝያ 18/2014 (ዋልታ) ከ10 ሺሕ በላይ ሰዎች የተሰተፉበት የኢፍጣር ፕሮግራም በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ተካሄደ።

የኢፍጣር ሂደቱ የሙስሊሙን አንድነትና በከተማዋ የሚገኙ የእምነት ተቋማትን አብሮነት ያሳየ ነው ተብሏል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ መሀመድ ኑሪዬ (ዶ/ር) የረመዳን ወር ሰዎች መልካም ሥራን የሚያበዙበት፣ ሰደቃ የሚያወጡበትና በእዝናት በምህረት ታጅበው አቅመ ደካሞችን የሚያስታውሱበት የተቀደሰ ወር በመሆኑ ሁሉም ሙስሊም አቅመ ደካሞችን ሊደግፍ ይገባል ብለዋል።

የቁሊቶ ከተማ ከንቲባ ሀሩና አሕመድ ከተማዋ በእምነት ውህድ ደምቃ፣ በአብሮነት ሰበዝ ተገምዳ፣ በመከባበር ሁሉን አክብራና ተከብራ ዛሬን የደረሰችው በሕዝቦቿ የሠላም አምባሳደርነት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከስልጤ፣ ጉራጌ፣ ሀዲያና ሌሎች አጎራባች ዞኖች የመጡ እንግዶችም በኢፍጣር ፕሮግራሙ መሳተፋቸውን የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን የላከልን መረጃ አመላክቷል።

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!