ባንኩ ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

ሚያዝያ 18/2014 (ዋልታ) ዳሽን ባንክ ከኤግል ላየን ቴክኖሎጂ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ።

ባንኩ ከኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር “ዱቤ ፔይ” በተሰኘ መተግበሪያ አማካኝነት ለደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ነው የተፈራረመው።

መተግበሪያው የንግድ ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን ለሸማቾቹ በዱቤ ማቅረብ እንዲያስችላቸው የሚያደርግ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ሸማቾች የሚያጋጥማቸውን ጊዜያዊ የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍና ያሉባቸውን ክፍያዎች በቴክኖሎጂ በመታገዝ እንዲፈፅሙ የሚያደርግ እንደሆነ ተጠቁሟል።

በሱራፌል መንግሥቴ