ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ከዩኒሴፍ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

ሚያዝያ 20/2014 (ዋልታ) ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከሦስት ወራት በፊት የዩኒሴፍ ኤግዜኪዩቲቭ ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙትን ካትሪን ራስል በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የጉብኝታቸው ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ በርካታ ሕጻናትን ሁኔታ በቦታው ተገኝቶ ለማየትና ለመርዳት የሚያስችላቸውን የዓለም ዐቀፍ ከፍተኛ ድጋፍ ለማስገኘት ነው ተብሏል።

ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የመስክ ሥራ ልምድ ያለው ሲሆን ግንኙነቱን በማሻሻልና በመጠናከር መሠራት እንዳለበት ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ መግለፃቸውን ከጽሕፈት ቤታቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW