ቦይንግ 767 የመንገደኛ አውሮፕላንን ወደ እቃ ጫኝነት የመቀየር ሥራ በ2 ወራት ይጠናቀቃል

ሚያዝያ 21/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥገና ክፍል ቦይንግ 767 የመንገደኛ አውሮፕላንን ሙሉ በሙሉ ወደ እቃ ጫኝነት የመቀየር ሥራን በሁለት ወራት ውስጥ እንደሚያጠናቅቅ አስታወቀ፡፡

የአየር መንገዱ የአውሮፕላን ጥገና ክፍል ከእስራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪስ (IAI) ጋር በጥምረት ቦይንግ የመቀየሩን ሥራ ማገባደዱን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ወደ እቃ ጫኝ የመቀየሩ ተግባር ሲጠናቀቅ የአየር መንገድ የጥገና ክፍል በአፍሪካ ደረጃ የመንገደኛ አውሮፕላንን ሙሉ በሙሉ ወደ እቃ ጭነት አውሮፕላን የቀየረ የመጀመሪያው የጥገና ማዕከል ያደርገዋል ተብሏል፡፡