የሰብአዊ ድጋፍ የያዙ 146 ተሽከርካሪዎችን ወደ ትግራይ ገብተዋል – መንግሥት

ሚያዚያ 21/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያዊ የተኩስ ማቆም ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ 146 የሰብአዊ ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎችን ወደ ትግራይ መግባታቸው ተገለጸ፡፡

ወደ ትግራይ ክልል ከሄዱት መካከል ዘጠኙ የነዳጅ ቦቴዎች ናቸው ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንቱ የተከናወኑ ዲፕሎማሲያዊ ሁነቶችን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን ማብራርያ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት የማቆም ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ ወደ ትግራይ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ያለገደብ እየገቡ ነው ብለዋል።

የተፈለገውን ያህል ድጋፍ የሚያደርግ የተራድኦ ድርጅት አለመኖርና ትሕነግ አሁንም በአፋርና በአማራ ክልል አንዳንድ ወረዳዎችን በወረራ መያዙ የሰብአዊ ድጋፉ የታለመለትን ያህል እንዳይሳካ ማድረጋቸው ተገልጿል ።

በሌላም በኩል በሶማሌ፣ ኦሮሚያና አፋር ክልሎች የዝናብ እጥረትን ተከትሎ በተከሰተው የምግብ እጥረት ሌሎች ድጋፍ የሚሹ ዜጎች እንዲኖሩ በማድረጉ የእርዳታ እጥረት እንደሚያጋጥም ተገልጿል ።

ከኢድ እስከ ኢድ በሚለው መርኃግብር ዲያስፖራውን ለሀገር አንዲጠቅም በማድረግ በኩል አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ለሎሎች በዓላትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ከሳኡዱ አረቢያ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለሱ ሂደት እስካሁን 15 ሺህ 300 ኢትዮጵያን ተመልሰዋል ተብሏል።

በመስከረም ቸርነት