1443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በስልጤ ዞን እየተከበረ ነው

ሚያዝያ 24/2014 (ዋልታ) 1 ሺሕ 443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በስልጤ ዞን በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዞኑ በዓሉ እየተከበረባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ወራቤ ከተማ አንዷ ሲትሆን የእምነቱ ተከታዮች ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በተክቢራ በከተማዋ ወደ ሚገኘው ስታዲየም በመገኘት በዓሉን እያከበሩ መሆኑን ከሲልጤ ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth