ሚያዝያ 25/2014 (ዋልታ) ዛሬ ማለዳውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አጎራባች አካባቢዎች ከተውጣጡ በዝቅተኛ ገቢ ከሚተዳደሩ የማኅበረሰብ አባላት ጋር የማዕድ ማጋራት መርኃ ግብር ተካሄደ።
በማዕድ ማጋራቱ ወቅት በጽሕፈት ቤቱ ቅጥር ግቢ በጓሮ ግብርና አማካኝነት የበቀሉ አትክልቶች እንዲሁም ሰፊ ስፍራ በሌለበት የጓሮ ግብርና ለማካሄድ የሚያስችል መገልገያ መሰጠቱም ተጠቁሟል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አለምጸሐይ ጳውሎስ ተሳታፊዎቹን በጽሕፈት ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚካሄዱትን የጓሮ ግብርና ሥራዎች በመመልከት ግንዛቤ ወስደው ‘ምግባችን በጓሯችን’ በተሰኘው የጓሮ ግብርና እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ማበረታታቸውንም ከጽሕፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!