የጤና ሚኒስትሯ የጊኒ ዎርም በሽታን ለማጥፋት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለመታዘብ ጋምቤላ ገቡ

ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የጊኒ ዎርም በሽታን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለመታዘብ ጋምቤላ ክልል ገቡ፡፡
ሚኒስትሯ ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ዶክተር ሊያ በሁለት ቀናት በሚኖራቸው ቆይታ የጊኒ ዎርም ስርጭት በተደጋጋሚ በሚከሰትባቸው በጎግ እና አቦቦ ወረዳ የመስክ ምልከታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የጊኒ ዎርም በሽታን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝም ተጠቅሷል፡፡
በመስክ ምልከታው ላይ የጤና ሚኒስትሯ ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እና አጋር አካላት እንደሚሳተፉ ከጋምቤላ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!