የሳንቤ ጦርነት ድል በዓል እየተከበረ ነው

ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) የሳንቤ ጦርነት ድል በዓል በጎሬ ከተማ እየተከበረ ነው።

በወቅቱ የጣሊያን ወራሪ ኃይል ኢትዮጵያዊያንን ለመበቀል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ኢሉ አባ ቦራ ጎሬ ከተማን ለመቆጣጠር ተደራጅቶ ሲመጣ በሳምቤ ተራራ ላይ ድል ተደርጓል።

በወቅቱ በተደረገው ከባድ ውጊያ የኦሮሞ አርበኞች ያደረጉት ተጋድሎ በጎሬ ከተማ እየተዘከረ ይገኛል።

በዝክሩ ላይ የአካባቢው ተወላጆች እና ነዋሪዎች፣ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሰዓዳ ኡስማን እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዓሉ በ1928 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በነበረችው ጎሬ ከተማ በፓናል ውይይቶች እና ታሪካዊ ስፍራዎችን በመጎብኘት ይከበራል።

ሚልኪያስ አዱኛ (ከጎሬ)