ሸዋልን በሀረር ከግንቦት 1 እስከ 3 ይካሄዳል

ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) ሸዋልን በሀረር ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት 3 ቀን እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡
ከኢድ እስከ ኢድ ጥሪን ተከትሎ ከተዘጋጁ መርኃ ግብሮች መካከል “ሸዋልን በሀረር” እና በጅግጅጋ ከተማ የሚካሄደው ‘ሀገረ መንግሥት ግንባታና የዳያስፖራው ሚና’ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሲምፖዚየም ይገኙበታል፡፡
በጅግጅጋ ከተማ የሚካሄደው ሲምፖዚየም በመጭው ቅዳሜ ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ሸዋልን በሀረር ደግሞ ከግንቦት 1 እስከ ግንቦት ቀን 3 ድረስ በሀረር ከተማ ይካሄዳል።
በዚህም “ከኢድ እስከ ኢድ” ጥሪን ተከትሎ ወደ ሀገር ቤት የመጡ በመድረኮቹ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ዳያስፖራዎች ቀጥሎ በቀረቡት አድራሻዎች መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል፡፡
በስልክ ቁጥሮች (+251 965 34 55 33 ፤ +251 911 91 21 81 ፤ +251 911 46 55 30 ፤ +251 11 558 7473 ፤ +251 11 558 8355 ወይም በነጻ መስመር 9434) መደወል እንደሚችሉም ነው የተገለጸው፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!