ሚያዝያ 26/2014 (ዋልታ) በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ 1ሺሕ 29 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረብያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ዜጎች ውስጥ አምስት ህጻናትና 1ሺሕ 24 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ከ18 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡