በወላይታ የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሮኬት ሰራ

ሚያዝያ 28/2014 (ዋልታ) በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ተማሪ ኢ ቲ አር ኤስ1 ኬ ኤም የተባለ ሮኬት ሰራ።
ወጣት ሳሙኤል ዘካሪያስ በወላይታ ዞን የ11ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የገንዘብ ድጋፍና ትብብር ETR S1KM ተብሎ የሚጠራ ሮኬት መስራቱን በዛሬው እለት አስታውቋል።
ወጣት ሳሙኤል ከዚህ በፊት ከአከባቢው ያገኘውን የተለያዩ ቁሳቁስ በመጠቀም ኤክስካባተር መኪና እንዲሁም የቆሻሻ ማፈሻ መኪና ሰርቶ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ተሸላሚ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በቅርቡም የተሳካ የማስወንጨፍ ሙከራ እንደሚያደርግ ተመላክቷል።
ወጣቱ የሰራው ሮኬት አንድ ኪሎ ሜትር ድረስ የመወንጨፍ አቅም ያለው መሆኑንና ሮኬቱን የሚሸከመው መኪናም አብሮ መሰራቱ ታውቋል።
ለወጣት ሳሙኤል ዘካሪያስ የተደረገው ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል።