በዴንማርክ የልማትና ትብብር ሚኒስትር የተመራ ልዑክ ጎዴ ገባ

ሚያዝያ 29/2014 (ዋልታ) በዴንማርክ የልማትና ትብብር ሚኒስትር ፍሊሚንግ ሞለር ሞርቲንሰን የተመራ ቡድን ጎዴ ከተማ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ጎዴ ዑጋዝ ሜራድ ሊይሊ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርዕሠ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ልዑኩ በክልሉ የተከሰተው ድርቅ በኅብረተሰቡ ላይ ያደረሰውን እና የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ እንዲሁም ለድርቁ ምላሽ መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር እንደሚወያይ የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አስነብቧል፡፡
እንዲሁም በመሠረተ ልማት አቅርቦት ላይ ድጋፍ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይመክራል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!