መዲናዋን ውብ እና ፅዱ ለማድረግ ነዋሪው ተሳታፊ መሆን አለበት

ሚያዝያ 29/2014 (ዋልታ) አዲስ አበባን ውብ እና ፅዱ ለማድረግ የከተማዋ ነዋሪ በፅዳት እና ውበት ሥራ ባለቤት በመሆን መሳተፍ እንዳለበት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ አሳሰቡ።
በከተማዋ የሚስተዋለውን የፅዳት ሁኔታ ለመቀየር በኅብረተሰቡ ትብብር ለውጥ እንደሚመጣም ጠቅሰዋል።
በፅዳት ዘመቻው ዋና ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባን ውብ እና ፅዱ ለማድረግ አካባቢን በማፅዳት የተጀመረው በትምህርት፣ በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማትን የማፅዳት ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያሳያል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!