የበጋ የስንዴ ምርት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ

ሚያዝያ 30/2014 (ዋልታ) የበጋ የስንዴ ምርት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “በጋራ በቀደሙት ስኬቶቻችን ላይ አብሮ የከተማ ግብርና ታክሎበት የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ቀስ በቀስ መፍታት ያስችለናል” ብለዋል።