ጠ/ሚ ዐቢይ ዓመታዊ የቤት እድሳት መርኃ ግብር አስጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ግንቦት 1/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዓመታዊ የቤት እድሳት መርኃ ግብር ማስጀመራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ይፋ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዓመታዊ የቤት እድሳት መርኃ ግብር በምናስጀምርበት በዚህ ወቅት ግለሰቦች፣ የንግድ ተቋማት እና የመንግሥት ተቋማት ክረምት ከመግባቱ በፊት በአካባቢያችን ላሉ በርካታ ሰዎች ምቹ እና ሰብአዊ ክብርን መሠረት ያደረገ የኑሮ ሁኔታን ለመፍጠር በሚደረገው ዓመታዊ ክንውን የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ። በተለይም የንግድ ድርጅቶች ማኅበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ኑሮ ማሻሻል ይችላሉ” ብለዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW