የሸዋል ኢድ በዓል በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚደረገው ጥረት ከቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ከፍ ያደርገዋል ተባለ

ግንቦት 1/2014 (ዋልታ) የሸዋል ኢድ በዓል በዩኔስኮ ለማስመዝገብ የሚደረገው ጥረት ከቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ከፍ እንደሚያደርገው ተገለጸ፡፡
የሸዋል ኢድ በዓል በሀረሪ ክልል እየተከበረ ሲሆን ዋልታ ያነጋገራቸው የበዓሉ ተሳታፊዎች የዘንድሮ የሸዋል ኢድ በዓል አከባበር ሸዋል ኢድን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ በሚገኝበት ወቅት ማክበራችን ልዩ ስሜት ፈጥሮብናል ብለዋል፡፡
የሸዋል ኢድ በዓል ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ እየተከበረ መሆኑን የሚገልፁት ተሳታፊዎቹ በርካታ የክልሉ ዲያስፖራዎችና እንግዶች በዓሉን መታደማቸው የሀረርን ባህል፣ ታሪክና እሴት እንዲያውቁ ያደርጋቸዋል ብለዋል።
“ከኢድ እስከ ኢድ” መርኃ ግብር አካል የሆነው የሸዋል ኢድ በዓል በዩኔስኮ ለማስዝገብ የሚደረገው ጥረት ከቱሪዝም የሚገኘው ገቢ ከፍ እንደሚያደርግ ነው ተሳታፊዎቹ የገለፁት።
ዲያስፖራዎችና እንግዶች በዓሉን መታደማቸው የሀረርን ባህል፣ ታሪክና እሴት እንዲያውቁ አድርጎናልም ብለዋል።
በርካታ እንግዶች በዓሉን መታደማቸው የበዓሉ ድባብ ይበልጥ እንዲያምር አድርጎታል ሲሉም የበዓሉ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
ሱራፌል መንግሥቴ (ከሀረር)