አሸባሪው አል-ሸባብ በድንበር አከባቢ የቀበረው በርካታ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

ግንቦት 2/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል እና የመረጃና ደኅንነት አካላት ባደረጉት የጋራ ዘመቻ አሸባሪው አል-ሸባብ በድንበር አካባቢ የቀበረው በርካታ ጦር መሳሪያ በቁጥጥር ሥር ዋለ፡፡
በሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ከሶማሊያ ድንበር አከባቢዎች የተሰማሩ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ሰራዊትና የመረጃ አካላት አሸባሪው አል-ሸባብ በድንበር ላይ ያከማቹት በርካታ ጦር መሳሪያዎች በባረይ ወረዳ በደዊ ቀበሌ ከ8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር አውለዋል።
በሶማሌ ክልል ልዩ ሁለተኛ ሪጅመንትና የመረጃና ደኅንነት አካላት ባደረጉት የጋራ ዘመቻ 50 AK 47 ወይም ክላሽ ኮቭ፣ 10 RPG መሳሪያዎችና ከ50 ሽጉጦችና በርካታ ጥይቶችን ያካተተ ህገ ወጥ መሳሪያ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም የልዩ ኃይል አመራሩ አሸባሪው አል-ሸባብ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ የደበቁት ጦር መሳሪያዎች የሽብር ጥቃቶች ለመፈጸም የተዘጋጁ እንደነበር ገልፀው ዒላማ ያደረጉት አከባቢዎች ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ማረጋገጣቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!