የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች ከሜዳው ውጭ እንዲያደርግ ተወሰነ

ግንቦት 2/2014 (ዋልታ) የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች ከሜዳው ውጭ እንዲያደርግ ወሳኔ አሳልፏል፡፡

ከስድስት ወራት በፊት ኢትዮጵያ በሜዳዋ ጨዋታዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል እና የካፍን ደረጃ የሚያሟላ ስታዲየም የላትም በሚል በሜዳዋ ማድረግ የሚገባትን ጨዋታዎች በገለልተኛ ሜዳ ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል።

ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላም በስታዲየሞቹ የተሻሻለ ነገር ባለመኖሩ ምክንያት ኢትዮጵያ በድጋሚ በሜዳዋ እንዳትጫወት ካፍ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህ ወር መገባደጃ ላይ ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳው እንዲጫወት እና የካፍ አመራሮችን ዝቅተኛ መስፈርት እንኳን ለማሟላት ርብርብ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካ መቅረቱ ታውቋል።

በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን በሜዳዋ እንድትጫወት ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን ካፍ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡