አፋን ኦሮሞ እና ትግርኛ በጉግል መተርጎሚያ ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጉግል አፋን ኦሮሞ እና ትግርኛ ጨምሮ ከ300 ሚሊዮን በላይ በሆኑ ሰዎች የሚነገሩ 24 ቋንቋዎች በጉግል መተርጎሚያ ዝርዝሩ ውስጥ አካተተ፡፡
ኩባንያው በመተርጎሚያ ዝርዝሩ ባካተተው አዳዲስ ቋንቋዎች ውስጥ አስሩ በአፍሪካ የሚነገሩ ሲሆን አፋን ኦሮሞ ፣ ትግርኛ፣ ትዊ፣ ባምባራ፣ ክሪዎ፣ ሉጋንዳ ይገኙበታል፡፡
አፋን ኦሮሞ በኢትዮጵያ እና በኬንያ እንዲሁም ትግርኛ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ በስፋት የሚነገሩ ቋንቋዎች ናቸው፡፡
አዲስ የተካተቱት ቋንቋዎች በጉግል ተርጓሚ የተካተቱ አጠቃላይ ቋንቋዎች ብዛት ወደ 133 ከፍ አድርጎታል፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!