በብሔራዊ ምክክሩ ላይ የሚዲያ ሚና ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተገለፀ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሽግግርና ብሔራዊ ምክክር ላይ የሚዲያ ሚና ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተገለፀ።
በጅማ፣ ባሕር ዳርና ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲዎች አዘጋጅነት ሚዲያ ላይ ያተኮረ የባለ ድርሻ አካላት ውይይት እየተካሄደ ነው።
ሚዲያ በህግ የበላይነትና ዲሞክራሲ ግንባታ ላይ ወሳኝ ሚና እንዳለው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ኤሊያስ አሊ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
የኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ገረመው ሁሉቃ (ዶ/ር) በበኩላቸው ሚዲያ በሀገራዊ ምክክር ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው በማብራራት ከመድረኩ በርካታ የመፍትሄ ምክረ ሀሳቦች እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው የውይይት መድረክ ላይ የውጭ ሀገራት ምሁራን እየተሳተፉ ሲሆን በመድረኩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ምክክርና ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በደምሰው በነበሩ