የኢትዮጵያ ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ አስገኘ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማስገኘቱን የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን አሰታወቁ።

ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት የኢትዮጲያ ቡና በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአስር ወር ውስጥ የአንድ ቢልየን ዶለር የውጭ ምንዛሬ አስገኝቷል ብለዋል።

እ.ኤ.አ በ2020 ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ ከምታቀርበው የቡና ምርት 860 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ያገኘች ሲሆን ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ ፣ ጀርመን እንዲሁም ጃፓን የኢትዮጵያ ቡና ወደ ሀገራቸው በማስገባት ግንባር ቀደም ሀገራት መሆናቸው ይታወቃል፡፡