ሀሰን ሼክ መሃመድ 10ኛው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ሀሰን ሼክ መሃመድ

ግንቦት 8/2014 (ዋልታ) ሀሰን ሼክ መሃመድ 10ኛው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ተገለጸ።

በሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሰፊ የድምፅ ልዩነት ያሸነፉት ሀሰን ሼክ መሃመድ ምርጫው በተጠናቀቀ ጥቂት ሰዓታት ውስጥ 10ኛው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።

ለሁለት ዓመታት የተራዘመው የሶማሊያ ምርጫ በትላንትናው እለት ተካሂዶ አገሪቱን ለቀጣይ 4 ዓመታት የሚመሩት ሀሰን ሼክ መሃመድ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በ3ኛው ዙር 328 ድምፅ ያለው የሶማሊያ ፓርላማ ባደረገው ምርጫ ሀሰን ሼክ መሃመድ በስልጣን ላይ ያሉትን መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆን ካጠቃላዩ ድምፅ የ214ቱን በማግኘት ነው ለማሸነፍ የቻሉት።

መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ 110 ድምፅ ያገኙ ሲሆን አንድ ሰው ደግሞ ድምፅ አለመስጠቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሶማሊያው ተመራጭ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ ከ2012 እስከ 2017 ሶማሊያን በፕሬዝዳንትነት መርተው እንደነበረ ይታወሳል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!