ጠ/ሚ ዐቢይ ለተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ግንቦት 8/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት በደስታ መልዕክታቸው “ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ በድጋሚ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጥዎ እንኳን ደስ ያለዎት ለማለት እወዳለሁ” ብለዋል።

የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበን እንደምንሠራ እምነቴ ነው ሲሉም ለፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት አክለዋል።

የሶማሊያው ተመራጩ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ ከ2012 እስከ 2017 ሶማሊያን በፕሬዝዳንትነት መርተው እንደነበረ ይታወሳል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW