የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲስ ተመራጩ ፕሬዚዳንት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ

ግንቦት 8/2014 (ዋልታ) የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲስ ተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የእንኳን ደስ አለህ መልእክት አስተላልፈዋል።

መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በቲውተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት “ወንድሜ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ 10ኛው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሆነህ በመመረጥህ እንኳን ደስ አለህ” ብለዋል።

መላው የሶማሊያ ሕዝብም ለአዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ እና ለስኬታቸውም እንዲፀልዩ አብዱላሂ ፋርማጆ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሁሉ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW