የአባቶች ቀን ከግንቦት 15 እስከ 19 ይከበራል

ግንቦት 8/2014 (ዋልታ) ዘንድሮ የሚከበረው የአባቶች ቀን “ክብርና ምስጋና ትውልድን በማተካካት አገራችንን ለሠሯት አባቶች” በሚል መሪ ቃል ከግንቦት 15 እስከ ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚከበር የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ለ5 ተከታታይ ቀናት በመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከሚረዱ አባቶች፣ ከወጣቱ ትውልድ እና ከተለያዩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር በመሆን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።

ለአንድ አባት አንድ ምሳ ማብላት እንዲቻል ለበዓሉ የተዘጋጁትን ፖስት- ካርዶች አንዱን በ100 ብር በመግዛት ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረቡን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የበዓሉ አንዱ አካል በሆነው 1000 አባቶችን ጋቢ የማልበስ መርሐ- ግብር ላይ ከአንድ ሰው ጀምሮ የተቻልዎትን ያህል ጋቢ በማምጣት በይፋ አባቶችን ጋቢ እንዲያለብሱ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።