ማዕከላዊ ዕዝ አሸባሪዎችን መደምሰስ በሚያስችል ወታደራዊ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

ግንቦት 9/2014 (ዋልታ) ማዕከላዊ ዕዝ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩ አሸባሪዎችን መደምሰስ በሚያስችል ወታደራዊ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ማዕከላዊ ዕዝ “ስልጠና ለተሻለ የግዳጅ አፈፃፀም” በሚል መርህ በተሠጠው የአመራር ስልጠና በምንም የማይበገር አዋጊና ተዋጊ አባላት ማፍራት እንደተቻለ የዕዙ ዋና አዛዥ ሌ/ጀኔራል ዘውዱ በላይ አረጋግጠዋል።

“በሳል አመራር ብቁ ተዋጊ የሠራዊት አባላትን ለማፍራት አይቸገርም” ያሉት ሌ/ጀኔራሉ የማዕከላዊ ዕዝ አመራሮች የሠራዊቱን ሞራላዊና ሥነ-ልቦናዊ ዝግጁነት በመገንባት ለማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።

“ዕዙ በአሁኑ ሰዓት የታጠቀው መሣሪያ ብቻ ሳይሆን የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና ጭምር ነው” ያሉት ደግሞ በዕዙ የኮር ዋና አዛዥ ብ/ጀኔራል ተስፋዬ ረጋሳ በስልጠና የተገኘውን የተሟላ ዝግጁነት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

የማዕከላዊ ዕዝ በተሰጠው የግዳጅ ቀጣና በሀገሪቱ ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩ አሸባሪዎችን መደምሰስ በሚያስችለው አስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም መገለፁን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW