146 ኢትዮጵያዊያን ከየመን ተመለሱ

ግንቦት 9/2014 (ዋልታ) በአንድ ጊዜ በረራ 146 ኢትዮጵያዊያን ከየመን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ከተመለሱት መካከል 126 ወንዶች 15 ሴቶችና 5 ህጻናት እንደሚገኙበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡